Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዳይከበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዳይከበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጀኔራል ኮሚሽነር ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ እንደገለጹት÷ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዳይከበር ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ሰዎች በተጨማሪም የጦር መሳሪያ ተይዟል።

በዚህም 14 ክላሽ፣26 የእጅ ቦምብ እና 103 ሽጉጥ መያዙን ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ አያይዘውም  በዓሉ በሰላም እንዳይከበር ከኦነግ ሸኔ እና ከህወሀት ተልዕኮ በመቀበል የሚንቀሳቀሱ አካላትን ህብረተሰቡ በመጠቆምና ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ  የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ  አቅርበዋል ።

የኦሮሚያ ፖሊስ የሕዝቡን ሰላም የሚያውኩትን በመከታተል ሕግ ለማስከበር በቁርጠኝነት መዘጋጀቱንም ኮሚሽነሩ ማስታወቃቸውከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.