Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ጅቡቲ የዕንባ ጠባቂ ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያና ጅቡቲ የእንባ ጠባቂ ተቋማት በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሃይሌ እና የጅቡቲ የዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር ቃሲም ኢሳቅ ስምምነቱን ዛሬ ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሃይሌ እንዳሉት÷ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በጋራ መስራት የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።

ሃገራቱ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ከማጠናከርና በተለያዩ መስኮች ተቀራርበው እንዲሰሩ ከማድረግ አንጻርም ወሳኝ ሚና አለው ነው ያሉት።

የጅቡቲ የዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር ቃሲም ኢሳቅ በበኩላቸው÷ በስምምነቱ መሰረት የሁለቱ ተቋማት ባለሙያዎች የልምድ ልውውጦችን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እንዲያደርጉም በዶክተር ቃሲም ግብዣ እንደቀረበላቸው ኤዜአ ዘግቧል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.