Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን እና የሱዳንን ሕዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይገባል -አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን እና የሱዳንን ሕዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚገባ በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ገለጹ፡፡
አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ከሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ደፋኣላ አልሃጅ ጋር በኢትዮጵያና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በሁለቱ አገራት ሕዝቦች መካካል ያለው ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀና በመልክዓ ምድር፣ ባህል፣ ታሪክ እና ሃይማኖት የተሳሰረ መሆኑን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ አውስተዋል።
አክለውም በሁለቱ መንግስታት መካከል ልዩነቶች ቢከሰቱም እንኳ ዘላቂና ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻችንን ግምት ውስጥ በማስገባት በሰከነና በሰላማዊ መንገድ ልዩነቶችን ለመፍታት መስራት አስፈላጊ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
አምባሳደር ደፋኣላ አልሃጅ በበኩላቸው÷ የሁለቱን አገራት ሕዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሁለቱ መንግስታት መካካል የሚነሱ ልዩነቶችን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሱዳን ዝግጁ ናት ማለታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.