Fana: At a Speed of Life!

‘’የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ አሸናፊነት ያንፀባርቃል’’ የተባለ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በሀረር ከተማ ተከፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ስለ ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ ‘’የኢትዮጵያን ዘርፈ ብዙ አሸናፊነት ያንፀባርቃል’’ የተባለ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በሀረር ከተማ ተከፈተ።

አውደ ርዕዩን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ከፍተውታል።

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ከ1960ዎቹ ጀምሮ እስከ አሁን ያለውን ሁለንተናዊ ገፅታ በሚያሳይ መልኩ ለህዝብ እይታ መቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተለይም ኢትዮጵያውያን በህልውና ዘመቻው ያሳዩት ተጋድሎና ሀገርን ለማዳን የተከፈሉ መስዋዕትነቶችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎች ለዕይታ ቀርበዋል።

ከጅግጅጋና ድሬዳዋ ከተሞች ቀጥሎ ለ4 ቀናት በሀረር ከተማ በሚቆየው በዚህ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ላይ፥ የምስራቅ አጎራባች ክልሎች አመራሮች፣ ባለሀብቶች፣ አባገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.