Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የቆዳ ውጤቶች በአፍሪካ የማስተዋወቂያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን የቆዳ ውጤቶች በአፍሪካ የማስተዋወቂያ ውይይት አካሂዷል፡፡

”የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታ የቆዳ ውጤቶች” በሚል የኢትዮጵያ ቆዳ እና የቆዳ ውጤቶችን በአፍሪካ ገበያ ለማስተዋወቅ ያለመው የቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት ከካምፓላ፣ ፕሪቶሪያ፣ አቡጃ፣ አክራ እና ራባት ከሚገኙ የኢፌዴሪ ሚሲዮኖች ጋር ማካሄዱ ተነግሯል፡፡

በውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና ዳያስፖራ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ የሀገሪቱን የቆዳ ውጤቶች በአፍሪካ ሰፊ ገበያ እንዲያገኙ ለማድረግ ከማህበሩ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጃፓን መንግስት በጃፓን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ኤጀንሲ አማካኝነት ለፕሮጀክቱ መሳካት እያደረገ ላለው አስተዋፅኦ አመስግነዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ሚሲዮኖች በየሀገራቱ ያለውን የቆዳ ምርቶች የገበያ ፍላጎት የተመለከተ ጥናት አዘጋጅተው እንዲልኩም ጠይቀዋል፡፡

በጥናቱ መሰረት ሁለት ሀገራት ተመርጠው በጃፓን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ፕሮጀክት አማካይነት የንግድ አውደ ርዕይና ሌሎችም እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር እንደሚደረግም ነው የገለጹት፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ኢትዮጵያ በቆዳ ዘርፍ እምቅ አቅም ያላት በመሆኑ በዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ በተለይም በአፍሪካ ሃገራት ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የገበያ መዳረሻን ማስፋት እንደሚገባ መገለጹን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.