Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ፣ሱዳን ፣ ኬንያ ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ መሪዎች የጋራ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በ38ኛው አስቸኳይ የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ይገኛሉ።

በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር የተናጠል ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተናጠል ውይይቱ ባሻገር  ከሱዳን ፣ ኬንያ ፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ መሪዎች ጋር የጋራ ውይይት አካሂደዋል።

በትብብር መረጋጋትን ማስፈን ለቀጠናው እድገትና ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊትር ገፃቸው ላይ።

አስቸኳይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በጠረቤዛ ዙሪያ በመሰባሰበችን እና በመነጋገራችን ደስተኛ ነኝ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.