Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልዩ ተውህቦና ተሰጥኦ ት/ቤትን በቴክኖሎጂ ለማደራጀት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣የካቲት10፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴ ር የኢትዮጵያ ልዩ ተውህቦ እና ተሰጥኦ ትምህርት ቤትን በቴክኖሎጂ ለማደራጀት የሚያስችሉ የስምምነት ሰነድ ከኤች ኮምፒውተሪንግ እና ፕሪንቲንግ ሚድል ኢስት ከሚባል የቴክኖሎጂ ተቋም ጋር ተፈራረመ።

ስምምነቱ በቡራዩ በመገንባት ላይ ላለው የኢትዮጵያ የልዩ ተውህቦ እና ተሰጥኦ ትምህርት ቤትን በዘመናዊና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመማር ማስተማር ስርአትን ለመዘርጋት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ እና ከቴክኖሎጂ ተቋሙ ተወካይ ማቲው ቶም ስምምነቱን ፈርመውታል።

በስምምነቱ የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ ያካተተ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ የትምህርት ቤቱ መምህራንን በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ስራ ለመስራት የሚያስችል ስልጠና መስጠት ፣ የመማሪያ ክፍሎችን፣ የማስተማር ሂደቱን፣ የፈተና የቁጥጥር ስርአቱን እና መሰል ተግባራትን በቴክኖሎጂ ማደራጀት መካተቱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በትምህርት ቤቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የኢኖቬሽን ማዕከል ፣ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ሂሳብና ኢንጂነሪንግ ዞን እንዲሁም የፈጠራ ባለሙያዎችን ተግባር የሚያግዝ ኢኖቬሽን ላብራቶሪ የሚደራጅ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.