Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዘጠኝ የአልሸባብ ታጣቂዎችን ደመሰሰ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ሀይል ( አሚሶም)  ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት  የአልሸባብ ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ ዘጠኝ ታጣቂዎችን ደመሰሰ።

በሶማሊያ ደቡባዊ ምስራቅ በሰራዊቱ የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት ለመፈፀም ዝግጅት ሲያደርግ በነበረው አልሸባብ የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደው እርምጃ በጥቂቱ ዘጠኝ ታጣቂዎች ሲገደሉ ከ11 በላይ የሚሆኑት ቁስለኛ ሆነዋል ነው የተባለው።

በባይ ክልል የከሳህደር ከተማ አስተዳደር የደህንነት ምክትል ኮሚሽነር መሀመድ ሙክታር በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እርምጃ መውሰዱን አረጋግጠዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአልሸባብ ላይ ይህን እርምጃ በመውሰዱ ደስተኛ መሆናቸውን መግለፃቸውን ሚዲል ኢስት ሞኒተር እና ጋሮዌ ዘግበዋል።

የከሳህደር ከተማ አስተዳደር ኮሚሽነር  አብደራዛቅ  አብዲ አስተዳደራቸው እና የክልሉ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና በህብረቱ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አልሸባብ ጥቃት ሊያደርስ እንደሚችል መረጃው ደርሷቸው እንደነበረ ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.