Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከቻይናው ተቋራጭ ሲ ሲ ኢ ሲ ሲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ከቻይናው ተቋራጭ ሲ ሲ ኢ ሲ ሲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ የባቡር መስመርን አዋሽ ከሚገኘው የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፖ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ለመጫኛና ለማራገፊያ አገልግሎት የሚያስፈልጉ የተቋማት ግንባታን የሚያካትት ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ – ጅቡቲ የባቡር መስመርን ከአዋሽ – ኮምቦልቻ – ሀራ ገበያ የባቡር መስመር ጋር ከማገናኘት አንጻር ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።

የኮንትራት ስምምነቱ ከዲዛይን እስከ ግንባታ ያለውን የሚያጠቃልል ሆኖ 54 ነጥብ 93 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚሸፍን ሲሆን ወጪው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፍን ነው፡፡

95 በመቶ ነዳጅ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው በጅቡቲ ወደብ እንደመሆኑ መጠን ፕሮጀክቱ በተሽከሪካሪ ብቻ የሚመጣውን ነዳጅ በባቡር የትራንስፖርት አማራጭ እንዲገባ በማድረግና የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ነው የተባለው፡፡

ከአዋሽ ነዳጅ ማጠራቀሚያ የሚገኘውን ነዳጅ ወደ መሃል ሀገር ለማድረስም ፕሮጀክቱ አስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቅሷል።
የአዋሽ ብሔራዊ የነዳጅ ዴፖ እስከ 130 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ነዳጅ የመያዝ አቅም እንዳለው ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ፕሮጀክቱ በአንድ አመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.