Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 46 ታዳጊዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሞተር ስፖርት ውድድር ያሰለጠናቸውን 46 ታዳጊዎች አስመረቀ።
 
ማህበሩ በሁለት ዙር 60 ታዳጊ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲያሰለጥን የቆየ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 46ቱን ለምረቃ አብቅቷል።
 
ከተመራቂዎቹ መካከል አስሩ ሴቶች ሲሆኑ ሰላሳ ስድስቱ ወንዶች መሆናቸውም ታውቋል።
 
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፥ ኢትዮጵያ ካላት ልዩ ልዩ የመሬት አቀማመጥ አንፃር ኢትዮጵያ ለሞተር ስፖርት ናት፤ ታዳጊዎች ከስፖርቱ ባሻገር ለቴክኖሎጂ ቅርብ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ብለዋል።
 
መንግስት ለዘርፉ አሰራሩን በማመቻቸት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
 
የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አስራት ወርቁ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የሞተር ስፖርት ማህበር አባል ከሆነች ከ50 አመታት በላይ ቢቆጠርም በተለያዩ ምክንያቶች ስፖርቱ ተዳክሞ ቆይቷል ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ የሞተር ስፖርት መነቃቃት ለቱሪዝም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል።
 
ተመራቂዋች ለታዳሚያን የውድድት ትዕይንት ያቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም ለአሰልጣኞችና ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት መስጠታቸውን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.