Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሰላም ለአፍሪካ ቀንድ ደህንነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም በምክትል ዋና ፀሐፊ ማዕረግ በናይሮቢ የሚገኘው የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት ዋና ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ጄኔራል ከሆኑት ሀዋ ባንጉራ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ዳይሬክተር ጄኔራል ባንጉራ የኢትዮጵያ ሰላም ለአፍሪካ ቀንድ ደህንነት ወሳኝ መሆኑን ተናግረው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በተመሳሳይ አምባሳደር መለስ በኬንያ ከፊንላንድ አምባሳደር እርክ ላንድበርግ እና ከቡሩንዲ አምባሳደር ሀቦኒማና ኢቪሊን ጋር ተወያይተዋል።
በኢትዮጵያ እና በፊንላንድ መካከል ጠንካራ ወዳጅነት መኖሩን የተናገሩት አምባሳደር እርክ ላንድበርግይህንኑ ለማጠናከር በትብብር መስራት እንደሚገባ መግለፃቸውን ኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ አምባሳደር ኢቪሊን ጋር ቡሩንዲ እና ኢትዮጵያ የናይል ተፋሰስ አገሮች እንደመሆናቸው ከተቀሩት የወንዙ ተፋሰስ አገሮች ጋር በሚደረግ ትብብር ሁለቱ አገሮች ግንቢ ሚና መጫወት በሚችሉበት ዙርያ መክረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.