Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአየር ትራንስፖርት መስመር ዝርጋታ ስልጠና መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአየር ትራንስፖርት መስመር ዝርጋታ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
 
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው በአፍሪካ በራሳቸው የሰው ኃይል የሚያሰለጥኑ የሲቪል አቪዬሽን ተቋማት አለመኖራቸውን ጠቅሰው፥ በምዕራብ አፍሪካ ባለሙያዎችን ከውጭ ሀገራት በማስመጣት ስልጠናው ይሰጥ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
 
ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ጋር በመነጋገር ስልጠናውን ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እንዲሰጥ ፈቃድ ለማግኘት ይሞክራልም ብለዋል፡፡
 
ከዚህ ጎን ለጎን ከዚህ ቀደም በውጭ ሀገራት ሲሰጡ የነበሩ ሌሎች ስልጠናዎችን በሀገር ውስጥ ለመስጠት ጥረት እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡
 
ከ1944 ዓ.ም. ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ስልጠና ማዕከል ወደ አካዳሚነት ለማሳደግ ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም እየተገነባ ያለውና በቅርብ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው አዲሱ ህንፃ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው መናገራቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.