Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የ30 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አገኘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ጋር የ30 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ።

የድጋፍ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እና በኢትዮጵያ የዩኤስ አይ ዲ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ተፈራርመውታል።

ድጋፉ ቦርዱ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ተአማኒ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ይውላል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ፥ ድጋፉ ቦርዱ ቀጣዩን ሃገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የጀመረውን ጥረት ለማገዝ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

አያይዘውም ቦርዱ ምርጫውን ተአማኒ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፥ ጥረቱ እንዲሳካ ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የዩ ኤስ አይ ዲ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ በበኩላቸው፥ አሜሪካ ለቦርዱ የቴክኒክና የሰው ሃይል ማብቃትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እንደምታደርግ ገልጸዋል።

በሙሃመድ አሊ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.