Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስድስት ደረጃዎችን አሻሻለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በሚያወጣው ወርሃዊ የሃገራት የእግር ኳስ ደረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስድስት ደረጃዎችን አሻሻለ፡፡

ቡድኑ በወርሃዊው የሃገራት ደረጃ ከነበረበት 146ኛ ደረጃ 140ኛ ላይ መቀመጡን ፊፋ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ካሜሩን ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወሳል፡፡

ቤልጂየም፣ ፈረንሳይ እና ብራዚል ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ከአፍሪካ ሴኔጋል ሁለት ደረጃዎችን አሽቆልቁላ 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ቱኒዚያ 26ኛ ደረጃ በመያዝ ሁለተኛ ስትሆን ናይጄሪያ አራት ደረጃዎችን በማሻሻል 32ኛ ላይ ትገኛለች፡፡

ጊኒቢሳው 11 ደረጃዎችን በማሻሻል ቀዳሚ ስትሆን 108ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ናሚቢያ 10 ደረጃዎችን በማሻሻል 111ኛ ስትሆን አርመንያ 9 ደረጃዎችን በማሻሻል 90ኛ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በፊፋ ወርሃዊ የሃገራት ደረጃ ሞዛምቢክ 11 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል ቀዳሚ ስትሆን ወደ 117ኛ ደረጃ ተንሸራታለች፡፡

ኢስቶኒያ እና ሊቢያ 8 ደረጃዎችን ወርደው 116ኛ እና 119ኛ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ብሪቲሽ ቨርጅን አይላንድስ፣ ኧንጉይላ፣ ሳንማሪኖ ከ208ኛ እስከ 210ኛ ያለውን የመጨረሻዎቹን ደረጃዎች መያዛቸውን የፊፋ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.