Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአፍሪካ 2021 ምርጥ ማዕከላዊ አመራር ባንክ ሽልማት አገኘ

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአፍሪካ 2021 ምርጥ ማዕከላዊ አመራር ባንክ የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነ።

ባንኩ የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ የሆነው፣በተለይ ባለፉት ሁለት አመታት የሀገሪቱን የገንዘብ፣የውጭ ምንዛሬና የፋይናንስ ፓሊሲዎችን በመቅረጽ እንዲሁም የክፍያ ስርዓቱን የሚያሳልጡ አሰራሮችን በመንደፍና አተገባበራቸውን በመከታተል ለኢኮኖሚ ቀጣይ እድገትና ለህዝቦች የኑሮ ደረጃ መሻሻል የራሱን አስተዋጽኦ በማበርከቱ እንደሆነ ተገልጿል።

በእንግሊዝ ሀገር የሚገኘው ካፒታል ፋይናንስ ኢንተርናሽናል የህትመት ጆርናል ነው ባንኩን የሸለመው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 7.2 ሚሊየን አዲስ የቁጠባ አካውንት እና 110.8 ቢሊየን ብር አዲስ ተቀማጭ ሂሳብ ማፍራት ችሏል።

ኮቪድን ጨምሮ በርካታ ተግዳሮቶች ባሉበት ሁኔታ የመቋቋሚያ እና የማገገሚያ ስልቶችን በመንደፍ የኢኮኖሚ እድገት እንዲመዘገብ ድርሻው የጎላ እንደነበር ተገልጿል።

የቁጠባ ባህል እንዲያድግ ባንኩ የነደፋቸው እና ተግባራዊ ያደረጋቸው አሰራሮችም ውጤት አምጥተዋል።

በርካታ ተግባራት የሚቀሩት ቢሆንም ለስኬቱ መመዝገብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና በማቅረብ እንኳን ደሰ አላችሁ በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል በላከልን መግለጫ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.