Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ የኮረናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቋቋም የሚያስችል የገንዘብ ማሰባሰብ መርሃ ግብር ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 27፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ ትረስት ፈንድ የኮረናቫይረስ ወረርሽኝን ለመቋቋም የሚያስችል የገንዘብ ማሰባሰብ መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡
ገንዘቡ የሚያሰባስበው በኢንተርኔት አማካኝነት  መሆኑም ነው የተነገረው፡፡
ከዚያም ባለፈ ትረስት ፈንዱ ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 የከፋ ጉዳት ሳያደረስ ለመቋቋም ለምታደርገው ጥረት በመነሻነት 1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠትም ወስኗልም ነው የተባለው፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ በፌስ ቡክ ገጻቸው÷የትረስት ፈንዱ አማካሪ ምክር ቤት ለዚህ መልካም ተግባር የጀመረው ጥረት ያስመሰግነዋል ብለዋል፡፡
አምባሳደር ፍጹም ጋን በጠጠር ይደገፋል፣ኮሮና ቫይረስም በተባበረ ክንድ ይሸነፋል ብለዋል፡፡
ስለሆነም ኮሮናቫይረስን ወረርሽኝን ለማሸነፍ ይህን መልካም ጥረት መደገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.