Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገ በአዲስ አበባ በተመረጡ ቅርንጫፎች አግልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በነገው እለት እሁድ መስከረም 10 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተመረጡ ቅርንጫፎች አግልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ።
ባንኩ አዲሱ የብር ኖት ስርጭት መጀመርን በማስመልከት አገልግሎቱን እንደሚሰጥም ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ነባሮቹን የብር ኖቶች በአዲሶቹ የብር ኖቶች የመቀየር ሥራ መጀመሩ ይታወቃል።
ደንበኞች እስከ 5 ሺህ ብር ድረስ መቀየር የሚችሉ መሆኑን ያስታወቀው ባንኩ፥ ከዛ በላይ ሲቀይሩ ሂሳብ ካላቸው ወደ ሂሳባቸው ማስገባት ሂሳብ ከሌላቸውም አዲስ ሂሳብ ከፍተው ማስገባት ስለሚኖርባቸው ህጋዊ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርጫፍ የሚገኙት ኤቲኤም ማሽኖች በአዲሶቹ የብር ኖቶች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ መሆኑንም ባንኩመግለፁ ይታወሳል።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉም የባንኩ ኤቲኤም ማሽኖች ተመሳሳይ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉም ብሏል ባንኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.