Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ” የሽልማት መርሀ-ግብር ዕጣ ወጣ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ20ኛ ጊዜ ያዘጋጀው የ“ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ” የሽልማት መርሀ-ግብር ዕጣ በይፋ ወጥቷል፡፡
20ኛው ዙር የ“ይቀበሉ፤ ይመንዝሩ፤ ይሸለሙ” መርሀ-ግብር ከመጋቢት 15 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።
በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ከውጭ የተላከላቸውን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የተቀበሉ፣ በባንኩ በስዊፍት አድራሻ CBETETAA ከውጭ ገንዘብ የተላከላቸው እንዲሁም በባንኩ ቅርንጫፎች የውጭ ሀገር ገንዘብ የመነዘሩ ደንበኞች በዕጣው ውስጥ መካተታቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡
ዕጣው በዛሬው እለት ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በተወከሉ ታዛቢዎች ፊት የወጣ ሲሆን፣ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል የሚያስገኘው 1ኛው ዕጣ ቁጥር 7834834 ሆኗል።
በ2ኛ ዕጣ ባለሶስት እግር ተሸከርካሪ የሚያስገኙት ሁለት የዕጣ ቁጥሮች ደግሞ 7823760 እና 7906474 በመሆን ወጥተዋል።
ይህ መርሃ ግብር ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸውን ገንዘብ በህጋዊ መልኩ በባንክ በኩል እንዲያደርጉና እንዲመነዝሩ ለማበረታታት እና በባንኩ በተለይ በዓላትን በመንተራስ የሚዘጋጅ መሆኑ ታውቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.