Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9ኛ ዙር የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ” መርሀ-ግብር የእጣ ወጣ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ላለፉት 9 ወራት ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 9ኛ ዙር የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ”  የሽልማ መርሀ-ግብር ዕጣ በብሔራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በይፋ ወጥቷል።

የባንኩን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የባንኩ አመራሮች፣ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሀላፊዎች እና ተወካዮች፣ ደንበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ነው እጣው የወጣው።

በዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ፥ የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ” የቆጣቢዎች የሽልማት መርሀ-ግብር በርካቶች ወደ ባንክ አገልግሎት እንዲሳቡና የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያዳብሩ ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገ ገልጸዋል።

መጋቢት 2004 ዓ.ም የተጀመረው የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ” መርሀ-ግብር በሀብት ማሰባሰብ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ አቶ አቤ አክለው ገልፀዋል፡፡

ለ9 ዙሮች በተካሄደው የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!”  መርሀ-ግብር መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ደንበኞቻችንን የታላላቅ ሽልማቶች እድለኛ አድርጓል።

በታዛቢዎች ፊት በወጣው 9ኛው ዙር የሽልማት መርሀ-ግብር ዕጣ 2 ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርታማዎች፣ 3 መለስተኛ የጭነት ተሽከርካሪዎች፣ 15 ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎች እና 30 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች በአጠቃላይ 50 ሽልማቶች ለእድለኞች ደርሰዋል።

በዚህ መሠረት፡

  • በ1ኛ እጣ 2 አፓርታማ ቤቶች የሚያስገኙት የዕጣ ቁጥሮች 0000311398898 እና 0382600157224፤ እንዲሁም
  • በ2ኛ ዕጣ 3 መለስተኛ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሚያስገኙት የዕጣ ቁጥሮች 0034700387640 ፣ 0000762333420 እና 0167600256722 በመሆን ወጥተዋል።

ከታህሳስ 23 ቀን 2012 እስከ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ከብር 500 ጀምሮ በመቆጠብ የእድል ኩፖን ቁጥር ያገኙ ደንበኞች ተሳታፊ መሆናቸውንም ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.