Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎችም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ነው መግለጫው የሰጠው፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና ሌሎችም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት ነው መግለጫው የተሰጠው፡፡

በመግለጫው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ዝግጅትን፣ 50ኛ ዓመት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል አከባበር እንዲሁም ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ስላለው አለመግባባት ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ጋዜጣዊ መግለጫው የቶኪዮ 2020 ዝግጅትን የተመለከተውና እየተንከባለለ ስለመጣውና ሊቀረፍ ስላልቻለው ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ያለው ቅራኔም ዋነኛው ስለመሆኑም ተገልጿል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉና ሌሎች በመድረኩ የነበሩት አባላት አፅንኦት ሰጥተው ሲናገሩ የነበረው “ለቶኪዮ 2020 ዝግጅት አትሌቶች ሆቴል መግባታቸው የሚታወቅ ቢሆንም አትሌቶች በወቅቱ ሊሟላላቸው የሚገቡና የስልጠናው ዋና አካል የሆኑ መሠረታዊ ግብአቶች አለመሟላትን አንስተዋል፡፡

የአሰራር ክፍተቶች ከመፍታት ይልቅ ችግሮች እየተባባሱ በመሄዳቸው እና ይህ ጉዳይ ደግሞ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጎጂ እየሆኑ ያሉት አትሌቶችና አሰልጣኞች መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከዚህ በፊት በፌዴሬሽኑ ስራ ጣልቃ እንዳይገባና የአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ መተዳደሪያ ደንብን እንዲያከብር መጠየቁንም አስታውሰዋል፡፡

ሆኖም “ችግሩን ከመቅረፍ ይልቅ ጫና እየፈጠረብን በመምጣቱና” ይህም በአትሌቶቻችንና አሰልጣኞቻችን ላይም ችግሩ እየከፋ በመሄዱ የሚመለከተው አካል፣ መንግስትና ባለድርሻ አካላት ፌዴሬሽኑ በኦሎምፒክ ኮሚቴው ከመስመር የወጣ አሰራር ምክንያት እየደረሰበት ያለውን ችግር እንዲያውቅልን እንፈልጋለን” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሰልጣኞች፣ የቴክኒክ ባለሙያዎችና አትሌቶች የተገኙ ሲሆን ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ከመድረኩ ምላሽ መሰጠቱን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.