Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቶጎ ሎሜ በኩል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ አዲስ በረራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ በቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቶጎ ሎሜ በኩል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ አዲስ በረራ ዛሬ ጀመረ።

ከዚህ ቀደም አየር መንገዱ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ  በአየርላንድ ደብሊን አድርጎ በረራ ያደርግ ነበር ያሉት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሠው፥ የዛሬው አዲስ  የበረራ መስመር አፍሪካን ከአሜሪካ ለማገናኘት ይረዳል ብለዋል።

አየር መንገዱ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከፈረንጆቹ 1998 ጀምሮ በመብረር ላይ ነው።

በሎሜ በኩል የሚደረገው በረራ በቦይንግ 787 አውሮፕላን እንደሚደረግም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 116 ዓለም አቀፍ እና 23 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዳሉት መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን ይመልከቱ:-

 

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.