Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች የአፍሪካ ምርጥ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2021 የቢዝነስ ተጓዦች ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ ሽልማት አሸናፊ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በአፍሪካ ግዙፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ÷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆነው ”ቢዝነስ ትራቭለርስ ” መጽሄት የሚያዘጋጀውን ሽልማት ነው በምርጥነት ያሸነፈው።
የዚህ ዓመት ሽልማት የ24 ወራት የደንበኞች ምልከታ የሸፈነ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህ ዓመት በንግድ ተጓዦች የተሰጡ ድምጾች÷ የአየር መንገዶችን የተግባቦትና የኮሮና ወረርሽኝ የጥንቃቄ እርምጃዎች ውጤታማነት ታሳቢ ያደረጉ መሆኑም ተገልጿል።
በተሳፋሪዎች አያያዝ፣ በሚጣልበት እምነት እና የቲኬት ለውጦችን በማድረግ ረገድ የሚኖረው ተባባሪነት የወረርሽኙን ጊዜ ታሳቢ ያደረጉ ጥያቄዎች በሽልማት መስፈርትነት መካተታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ይህ የላቀ ሽልማት የአየር መንገዱ የደንበኞች እርካታ ነጸብራቅ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተናግረዋል፡፡
ሽልማቱ አየር መንገዱ በሁሉም ቦታ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ለማድረስ የሚያደርገውን ጥረት ስኬት የሚያሳይ በመሆኑ የሚያስደስት ነው ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.