Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለሚያስገነባው ባለ 36 ወለል ህንፃ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለዋና መስሪያ ቤት ባለ 36 ወለል ህንፃ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡
 
በመርሃ ግብሩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ አገልግሎት ስራ አመራር ቢርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያን ጨምሮ ሌሎች የከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
 
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፥ ህንፃው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈና ተወዳዳሪ አገልግሎት ለመስጠት ከሚኖረው ፋይዳ በተጨማሪ ለከተማውም ውበት በመሆን ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
 
የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ በዚህ ወቅት ከዋናው መስሪያ ቤት ጀምሮ በየደረጃው ያሉ ቢሮዎች አብዛኞቹ ለሠራተኞም ሆነ ለደንበኞች ምቹ ካለመሆናቸው በተጨማሪ የኪራይ ወጪው በተቋሙ ፋይናንስ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል ብለዋል።
 
ይህንንም ለመቅረፍ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የሚቀመጥለት ለዋናው መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚሰጠውን ህንጻ ጨምሮ 19 በመጀመሪያና 16 በሁለተኛ ምዕራፍ ተከፍሎ የሪጅን፣ የዲስትሪክትና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ቢሮ ግንባታ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መገባደዳቸውን ገልፀዋል።
 
ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም ተቋሙ የሚገለገልባቸው ቢሮዎች በተለያዩ ቦታዎች የተበታተኑ በመሆናቸው፤ ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው ህንጻ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።
መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ግንባታው በ4 አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቀው ይህ ህንፃ 4 ሺህ 500 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የሚያርፍ ሲሆን፥ የግቢው አጠቃላይ ስፋት 10 ሺህ 174 ካሬ ሜትር መሆኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላከታል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.