Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማእከልነት እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለጊዜያዊ የኮሮና ህሙማን ማገገሚያ ማዕከልነት እየተዘጋጀ መሆኑን የአካዳሚው የውድድር እና ስልጠና ዳይሬክተር አቶ አብዮት ተስፋዬ ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን ወደ ጊዜያዊ የኮሮና ቫይረስ ማገገሚያነት ለመቀየር እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚጠናቀቅ ኃላፊው ተናግረዋል።

የህክምና ባለሙያዎች ከአራት ቀናት በፊት ጀምሮ ማዕከሉን ለማረፊያነት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ዳይሬክተሩ ጨምረው ጠቁመዋል።

አካዳሚው በአስር የተለያዩ የስፖርት አይነቶች በጊቢው ውስጥ ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ከ300 በላይ ሰልጣኞችን በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሱን ኢቢሲ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.