Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ታህሳስ 3 ይጀምራል

አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ ይፋ አድርጓል።

የፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒው በኮቪድ ውስጥ ሆኖ የኢትጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለማስጀር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑንም አስታውቋል።

በዚህም ዝግጅቱን መሠረት በማድረግ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩ ታህሳስ 03 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ለተሳታፊ ክለቦች ማሳወቁን ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.