Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለሰላም እና ብሔራዊ መግባባት ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለሰላም እና ብሔራዊ መግባባት መሠረት ናቸው ባሏቸው ጉዳዮች ያደረጉትን ውይይት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በተያዘው ዓመት የሚደረገው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍ ከምርጫ በፊት፣ በምርጫ ሂደትም ሆነ ከምርጫ በኋላ ሁሉም ፓርቲዎች እና ባለድርሻ አካላት ሊያደረጉ የሚገቡ ጉዳዮችን የሚዳስስ ውይይት ከጥር 2 እስከ ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ባደረጉት ውይይት የጋራ መግባባት ላይ የደረሱባቸውን ነጥቦች በዝርዝር አቅርበዋል።

በቀረበው መግለጫ ከምርጫው በፊት እና በኋላ ሀገራዊ ሰላም እንዲጠበቅ ይበጃሉ ባሏቸው ጉዳዮች ላይ በጥልቀት መወያየታቸውን አስገንዝበዋል።

በሀገራዊ ሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ፣ የሰብአዊ መብት መከበር ጉዳይ፣ የመንግስት ሃላፊነት እና ተጠያቂነት ላይ የጋራ መግባባት መደረሱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የብሔረሰብ የማንነት ጥያቄ እና የምርጫ ክልል ተያያዥነት፣ በምርጫው ውጤት ሊነሡ ስለሚችሉ ጉዳዮች እና ተጠያቂነት፣ የፀጥታ አካላት ገለልተኝነት፣ የዴሞክራሲ ተቋማት ገለልተኝነት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና የተቋማት ገለልተኝነትም መግባባት ከተደረሰባቸው መካከል መሆናቸውን የሠላም ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል፡፡

የሚዲያ ተቋማት ገለልተኝነት፣ ምርጫው ፍትሐዊ እና ተአማኒ እንዲሆን የፖለቲካ ምኅዳሩን ስለማስፋት፣ የሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ የታሪክ እና ትርክት ጉዳይ፣ ብሔራዊ ዕርቅ በሚሉ ጉዳዮች ውይይት እንዳካሄዱባቸው እና የጋራ መግባባት ላይ እንደደረሱባቸው በመግለጫ አትተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.