Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ልዑካን ከሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የልዑካን ቡድን ከሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አካሄደ።

በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ደይሬክተር አቶ መሐመድ እንድሪስ የተመራው የልዑካን ቡድን ከሳዑዲ ዓረቢያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሚም አልደውሰሪ እንዲሁም ከልዩ ልዩ የሃገሪቱ ሚኒስትር መስሪያቤቶች ከተወከሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በወቅቱም በሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ ዜጎች መብትና ክብራቸው ተጠብቆ ስለሚኖሩበት ሁኔታ፣ የተመላሽና በማቆያ ማዕከላት ያሉ ዜጎች አያያዝ፣ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ዜጎች ችግር የሚፈታበት መንገድ፣ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አደጋዎች፣ የስራ ስምምነት ውል መፈራረም አስፈላጊነት እንዲሁም ወቅታዊ የሃገራችን ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት የተካሂዷል።

በውይይቱ በቀጣይ ለመንግስት ቀርበው ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮችም ተለይተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ከኢፌዴሪ የሪያድ ኤምባሲ ባልደረቦችና የኮሚኒቲ ተወካዮች ጋር ውይይት ከማድርጉም በላይ በሪያድ ዋፊድን አልሪያድና ስጂን አልሪያድ ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎችን መጎብኘቱን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.