Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ተቋም በኢትዮጵያ ህጋዊ ምዝገባ ማድረግ እንዲችል አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል-አምባሳደር ሬድዋን

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የኢትዮጵያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ተቋም የቦርድ አባላትን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
 
አባላቱ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እና የውሃ ሙሌትን አስመልክቶ በአረብኛ ቋንቋ በሚሰራጩ ሚዲያዎች ተገቢውን መረጃ በማቅረብ የተለየ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡
 
አምባሳደር ሬድዋን ተቋሙ የኢትዮጵያን ጥቅም በማስከበር በተለይም አትዮጵያ በታችኞቹ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ላይ የጎላ ጉዳት ሳታደርስ የውሃ ሀብቷን የመጠቀም መብት እንዳላት ለአረቡ ዓለም በአረብኛ ቋንቋ በማስረዳት ላደረጉት አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል።
 
በሚዲያዎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የበለጠ በማጠናከር መንግስት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር በማለም የሚያከናውናቸውን የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራዎች እንዲያግዙም ጠይቀዋል።
 
አባላቱ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ተቋማዊ ለማድረግ የሄዱበትን ርቀት ያደነቁት ሚኒስትር ዴኤታው፥በኢትዮጵያም ህጋዊ ምዝገባ ማድረግ እንዲችሉ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ተቋም በአረቡ ዓለም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስከበር እንቅስቃሴ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ በሚያካሂዱ ኢትዮጵያዊያን የቋቋመና በስዊዲን የተመዘገበ ተቋም ነው።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.