Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ዙር የካቲት 28 ቀን ይጀመራል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2ኛ ዙር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የሚጀመሩበትን ጊዜ አስታውቋል።

በዚህ መሰረት የሁለተኛው ዙር የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጀመሩ ፌዴሬሽኑ ለክለቦቹ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

15 ጨዋታዎችን ባስተናገደው የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ቅዱስ ጊዮርጊስ 28 ነጥብ በመያዝ በአንደኝነት አጠናቋል።

ፋሲል ከነማ በ26 ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ በ25 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ሀድያ ሆሳዕና፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና ድሬዳዋ ከተማ ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ሆነው የመጀመሪያውን ዙር ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.