Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ሩሲያ የጋራ ኮሚሽን በሀገራቱ መካከል የተደረሱ ስምምነቶች ያሉበትን ደረጃ ገመገመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያና የሩሲያ መንግስታት የጋራ ኮሚሽን በሁለቱ ሀገራት መካከል የተደረሱ ስምምነቶች ያሉበትን ደረጃ ገምግሟል።

የጋራ ኮሚሽኑ መሪዎች በኢኮኖሚ፣ በሳይንስ፣ ቴክኒክ እና የንግድ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ እና በሩሲያ ፌደሬሽን የተፈጥሮ ሃብትና የአካባቢ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትርና የፌደራል የማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ሃላፊ ኤቫግኒ ኪሰልቭ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተወያይተዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በፈረንጆቹ ጥቅምት 2019 ላይ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ የተስማሙባቸው ጉዳዮች ያሉበትን ደረጃ ገምግመዋል።

በዚህ ወቅትም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ኮሚሽኑ የጎላ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል የሚያስችላትን ስምምነት ማፅደቁን የጋራ ኮሚሽኑ አድንቋል።

በውይይቱ የኮሚሽኑ ስምንተኛውን የጋራ ስብስባ በፈረንጆቹ 2021 ላይ በአዲስ አበባ ለማድረግ መስማማታቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.