Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ አሜሪካ ቀጣይ ግንኙነት በጋራ መግባባት እና መከባበር ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በ ‘ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ’ ጋዜጣ ባሳተሙት “The way forward to Ethiopia-U.S. relations: Collaboration or confrontation?” የተሰኘ ፅሁፋቸው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የቆየ ግንኙነት በቀጣይ ምን ቅኝት መያዝ እንዳለበት አመላክተዋል፡፡

የጋራ ጥቅሞችን በትብብር በማሳደግ፣ የጋራ መግባባት በመያዝና በመከባበር ላይ በመመስረት የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የቆየ ግንኙነት የበለጠ በማሳደግ በፖሊሲዎችና በተቋማት ላይ ቀጥተኛ የሆነ በጎ ተጽዕኖን ማሳረፍ እንደሚቻል በፅሁፋቸው ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ውጪ ግን ለልማትና ለተለያዩ ፕሮግራሞች የተያዘን ድጋፍ በጊዜው አለመፈጸም ተራውን ዜጋ በእጅጉ ከመጉዳቱም በላይ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉ አይቀርም ነው ያሉት፡፡

የአሜሪካ ሴኔት በቅርቡ ያሳለፈው የውሳኔ ሃሳብ 97ም ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የማያግዝ መሆኑንም አቶ ደመቀ በፅሁፋቸው አንስተዋል፡፡

አሜሪካ በሌሎች ሉዓላዊ ሃገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የምትገባ ወይም በሃገራቱ አለመረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ ችግር እንዲፈጠር የምታደርግ ሆና መታየትን ማስወገድ ይኖርባታል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.