Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ጀርመን ሁለተኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮ ጀርመን ሁለተኛው  የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሄደ።
 
የሁለተኛው ዙር ሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ማስጀመሪያ ስብሰባ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና ደህንነት ዙሪያ በማተኮር ነው የተካሄደው።
 
ከዚህ ባለፈ ሚኒስትሮቹ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ፣ በአፍሪካ ቀንድ እና በአውሮፓ ቀጣናዊ ጉዳዮች እንዲሁም በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ሁለቱ ሀገራት በሚኖራቸው ትብብር ላይም መምከራቸውን በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
 
 
በቀጣይ ሳምንታትም የኢትዮ ጀርመን ግንኙነትን በኢኮኖሚ ጉዳዮች ፣ በማህበራዊ ልማት እና በሌሎች ዘርፎች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.