Fana: At a Speed of Life!

የኢንተርፖል የቀድሞው ሃላፊ የ13 ዓመት የእስር ቅጣት ተፈረደባቸው

አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ፖሊስ ተቋም (ኢንተርፖል) የቀድሞው ሃላፊ ሜንግ ሃንግዌይ  በቻይና የ13 ዓመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት ተፈረደባቸው።

የቻይና ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት ሜንግ በፈጸሙት የሙስና ወንጀል የ13 ዓመት ከስድስት ወር የእስር ቅጣት ውሳኔ አሳልፎባቸዋል።

ሜንግ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 ላይ ከኢንተርፖል ዋና መቀመጫ ፈረንሳይ ወደ ቻይና ከገቡ በኋላ ለተወሰኑ ቀናት ደብዛቸው ጠፍቶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

ከቀናት ቆይታ በኋላም ሜንግ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው  በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ቻይና አስታውቃ ነበር ።

የመጀመሪያ ቻይናዊ የኢንተር ፖል ሃላፊ የነበሩት የ56 ዓመቱ ሜንግ በምርመራ ሂደቱም ከሁለት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ጉቦ መቀበላቸውን ለፍርድ ቤት ማመናቸውም ይታወሳል።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው ፍርድ ቤትም  የዓለም አቀፋዊ ፖሊስ ተቋም የቀድሞው ሃላፊ ሜንግ ሃንግዌይ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም እና በፈጸሙት የሙስና ወንጀል የ13 ዓመት ከስድስት ወር እስር ቅጣት ወስኖባቸዋል።

ይህ ውሳኔ መተላለፉን ተከትሎ በፈረንሳይ ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩት የሜንግ ባለቤት  ውሳኔው ፖለቲካዊ ሴራ ያለበት ህገ ወጥ ድርጊት ነው ሲሉ ኮንነዋል ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.