Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ግብርና እና የተፈጥሮ ሃብት ውጤቶች አውደ ርዕይ በጅግጅጋ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የኢንዱስትሪ ግብርና እና የተፈጥሮ ሃብት ውጤቶች አውደ ርዕይ ተከፈተ፡፡
በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የኢንዱስትሪ፣ ግብርና እና የተፈጥሮ ሃብት ውጤቶች አውደ ርዕይ ዛሬ በይፋ በጅግጅጋ ተከፍቷል።
በአውደ ርዕዩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበልና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ማምጣት የሚቻለው በሁሉም አካባቢዎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ሲቻል ነው ብለዋል።
በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አቅም በአግባቡ ለመጠቀም ከአውደ ርዕዩ ጎን ለጎን ከፌዴራል የተዋቀረ ቡድን ከክልሉ ካቢኔ ጋር ምክክር ያደርጋል ብለዋል።
በሶማሌ ክልል እንዲህ አይነት አውደ ርዕይ ሲካሄድ የመጀመሪያው ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.