Fana: At a Speed of Life!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎችን በገንዘብ ለመደገፍ ከዩ.ኤን.ዲ.ፒ ጋር ተስማማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኮሮና ቫይረስ ዙርያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ.ኤን.ዲ.ፒ) ጋር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት መረፋፈሙን አስታወቀ።

ስምምነቱ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ የሚሰሩ ኢኖቬሽን ተኮር የምርምርና ፈጠራ ስራዎችን በገንዘብ ለመደገፍ የሚያስችል መሆኑንም ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

ስምምነቱ የተፈፀመው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ እና በኢትዮጵያ የዩኤንዲፒ ተወካይ ቱርሀን ሳለህ በቪዲዮ ኮንፈረንስ በታገዘ ከተወያዩ በኋላ ነው።

ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሲሳይ፥ ስምምነቱ የኮሮና ቫይረስን ለመለየት፣ ለመከላከልና ለማከም የሚደረጉ የተናጠል የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ጥረቶችን ለማቀናጀት የሚያስችል ማዕቀፍ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

በወረርሽኙ ዙሪያ የተለያዩ የፈጠራና ምርምር ስራዎች ያሏቸውን ባለሙያዎች መፍትሄዎቻቸውን በማወዳደር ጥቅም ላይ ለማዋልእንደሚረዳም ነው ያስታወቁት።

በስምምነቱ የ1 ሚልየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን፥ የፈጠራና ምርምር ስራዎቹ ድጋፉን የሚያገኙት በውድድር ሆኖ በእጭር ጊዜ ወደ ስራ ገብቶ በ3 ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው።

ማእቀፉ ከዚህ በፊት በሽታውን ለመከላከልና የህክምና ስራውን ለማገዝ በመንግስት፣ በግለሰቦችና በአጋር ድርጅቶች ሲደረጉ የነበሩ ድጋፎችን በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ ይረዳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.