Fana: At a Speed of Life!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ሱዳን መንገድን ጨምሮ በርካታ ቦታዎችን ተቆጣጠረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ማይዳሊ፣ ዳንሻ፣ ባዕከር፣ ልጉዲ፣ የሁመራ አየር ማረፊያ እንዲሁም የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ ገለጸ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሰራዊቱ በምዕራብ ግንባር እያደረገ ያለውን የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል።
ተገደው ለጽንፈኛው ቡድን ህወሃት እየተዋጉ የነበሩ በርካታ የትግራይ ልዩ ሃይል አባላት ለአገር መከላከያ ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ እንደሆነ ገልጸዋል።
አብዛኛው የልዩ ሃይል አባላት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑና ለወታደርነት ያልደረሱ መሆናቸውን የገለጹት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ፤ “ይህም ወደጦርነት የሚልካቸው ቡድን ለስልጣን እንጂ ለዜጎች ግድ የሌለው መሆኑን ያሳያል” ብለዋል።
ሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢ ያሉ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ለሰራዊቱ ያላቸውን ድጋፍና አለኝታነት በተግባር እያሳዩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.