Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅና ጠ/ሚ ዐቢይ ከፕሬዚደንት ኢሳያስ ጋር ተገናኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከኤርትራው ከፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ “ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በድጋሚ መጡ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል።

“ለሁለት ቀናት በሚያደርጉት ቆይታ፣ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እናደርጋለን፤ የዓለም አቀፋ ማኅበረሰብ አካል በመሆናችን ስለ ተጋፈጥናቸው ፈታኝ ሁኔታዎች እንወያይባቸዋለን” ሲሉም ገልፀዋል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

 
#FBC
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.