Fana: At a Speed of Life!

የኤፍ.ቢአ.ይ ኃላፊ ሩስያ አሜሪካ በቅርቡ በምታካሂደው ምርጫ ላይ ጣልቃ ለመግባት እየሞከረች ነው ሲሉ አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢአ.ይ) ኃላፊ  ክርስቶፈር ሬይ ሩስያ ዋሽንግተን በቅርቡ በምታካሂደው ምርጫ ላይ ጣልቃ ለመግባት እየሞከረች ነው ሲሉ አስጠነቀቁ፡፡

አሜሪካ በቅርቡ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዋን ለማድረግ እየተሰናዳች ትገኛለች፡፡

በሪፓብሊካኖቹ ወገን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም በዋይት ሃውስ ለመቆየት ይፎካከራሉ፡፡

በዲሞክራቶቹ ወገን የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እጩ ፕሬዚዳንት በመሆን ቀርበዋል፡፡

በዚህ ፕሬዚዳንታዊ ፉክክር ታዲያ ሩስያ የዲሞክራቱ እጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ላይ አነጣጥራለች ነው ያሉት ሬይ፡፡

ሩስያ ሐሰተኛ መረጃዎችንና ተገቢነት የሌላቸው ወቀሳዎችን እየነዛች እንደምትገኝም ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም አሜሪካውያን በምርጫ ሂደቱ መተማመን እንዳይኖራቸው የሚያደርግ ስራ እየሰራች ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሬይ ንግግር በነሃሴ ወር የብሄራዊ የጸጥታ እና ደህንነት መከላከያ ማዕከል በቅርቡ በሚካሄደው ምርጫ ዙሪያ ሩስያ፣ ቻይናና ኢራን ጣልቃ ለመግባት እየሞከሩ ነው ካሉ በኋላ የተሰማ ነው ተብሏል፡፡

በሃገሪቱ የሚገኙ የደህንነት ተቋማት በርካታ ሪፖርቶች ሩስያ በ2016ቱ ምርጫ ከዶናልድ ትራምፕ ጎን በመቆም በተቀናቃኛቸው ሂላሪ ክሊንተን ላይ ዘመቻ ከፍታ እንደነበር አረጋግጠዋል፡፡

 

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.