Fana: At a Speed of Life!

የእምቦጭ አረምን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ስትራቴጂክ እቅድ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእምቦጭ አረምን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ስትራቴጂክ እቅድ መዘጋጀቱን የጣና ሀይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር አያሌው ወንዴ እንደገለፁት፥ እምቦጭን ለማስወገድ ብዙ ጥረት ቢደረግም ስትራቴጅክ ፕላን ባለመኖሩ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አልተቻለም።

በያዝነው አመትም “ማጠናቀቅ” በሚል መሪ ቃል የአምስት አመት ስትራቴጅክ እቅድ በመዘርጋት እምቦጭን እስከ መጨረሻው ለማስወገድ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እቅዱ ውጤት እንዲያመጣም ለበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የመስሪያ ቁሶች እየቀረበ መሆኑንም አስረድተዋል።

በአንድ አመት ውስጥም የሚታየው የእምቦጭ አረም በማስወገድ በቀጣይ አዲስ የሚበቅለውን እንቦጭ የማጣራት ስራ ይሰራልም ነው ያሉት።

ከዚህ ባለፈም የውሀውን ክፍል በማፅዳት በሀይቁ ዳር ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከል የእንክብካቤ ስራዎች ይሰራሉ ማለታቸውን ከኢ.ፕ.ድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.