Fana: At a Speed of Life!

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያኢር ላፒድ በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ሊያደርጉ ነው፡፡

ሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው እንደ አዲስ ከጀመሩ ወዲህ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያ ነው፡፡

ሚኒስትሩ ከፊታችን ሰኔ 29 አስከ 30 በሚያካሂዱት ጉብኝትም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ከተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ጋር የሚመክሩ ይሆናል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የተገነባውን የእስራኤል ኤምባሲ መርቀው ይከፍታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ÷ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.