Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሚኒክ ራብ በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በመሆን እንግሊዝ በትምህርት ዘርፉ ድጋፍ ከምታደርግባቸው ፕሮጀክቶች መካከል በምስራቅ ጮራ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል።

በዚህ ወቅትም የኢትዮጵያን እና የእንግሊዝን ግንኙነት አስመልክቶ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ዶሚኒክ ራብ በቀጣይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጓዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዶሚኒክ ራብ በኬንያና ሱዳን ሲያደርጉት የነበረውን ጉብኝት አጠናቀው ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት።

በተስፋዬ ከበደ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.