Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 2 ቀን 2013 ዓ.ም ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የቀጣዩ የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መስከረም 2 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡

የሊጉ አስተዳዳሪ አካል የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በፈረንጆቹ መስከረም 12 በእኛ የአዲስ አመት ማግስት እንደሚጀመር አስታውቋል፡፡

በአውሮፓ የክለቦች ውድድር ተሳታፊ የሆኑ ክለቦች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት ቀን ግን እስካሁን አልተወሰነም፡፡

ክለቦቹ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና በዩሮፓ ሊግ እንግሊዝን ወክለው ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረጉ ጨዋታዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

ይህን ተከትሎም መስከረም ወር ላይ ለሚጀመረው ሊግ የሚኖራቸው የእረፍት ጊዜ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መቸ ይጫወቱ በሚለው ላይ አልተወሰነም፡፡

በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የተራዘመው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ መጠናቀቅ ይገባው ነበር፡፡

ከተራዘመ በኋላ በዝግ ስታዲየም ወደ ውድድር የተመለሰው ሊግ ከነገ በስቲያ በሚደረጉ የ38ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.