Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዛሬ በሚካሄደው 14ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሴናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

 

ሁለቱ ቡድኖች የ 5 ነጥብ ልዩነት ያላቸዉ ሲሆን÷ በጨዋታዉ የማይክል አርቴታ ቡድን የሚያሸነፍ ከሆነ ከቀያዮቹ ሰይጣኖች በ8 ነጥብ ይርቃል፤ ማንቸስተር ዩናይትድ የሚያሸንፍ ከሆነ ደግሞ የነጥብ ልዩነታቸዉ ወደ 2 የሚጠብ ይሆናል።

 

በማንቸስተር ዩናይትድ በኩል አምበሉ  ሃሪ ማጉዌር  ከቅጣት መልስ በጨዋታዉ የሚሰለፍ ሲሆን÷ የመሀል ተከላካዩ ራፋኤል ቫራን ከጨዋታው ውጪ  መሆኑ ተረጋግጧል።

 

በአርሴናል በኩል ቡካዮ ሳካ  ከጨዋታው ውጭ የመሆን እድል ሲኖረው÷ ግራናይት ዣካ እና ተከላካዩ ሴድ ኮላሲናክ ከጨዋታዉ  ውጭ  መሆናቸዉ ተረጋግጧል፡፡

 

በዉጤት ቀዉስ ዉሰጥ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ በኦልትራፎርድ ስታዲየም ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ ሲል ሰካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

 

በሚኪያስ አየለ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.