Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀምራል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀምራል።

ቀደም ብሎ ምሽት 2 ሰዓት ላይ አስተን ቪላ ሼፊልድ ዩናይትድን የሚያስተናግድ ይሆናል።

ምሽት 4 ሰዓት ከ15 ላይ ደግሞ ማንቼስተር ሲቲ አርሰናልን ያስተናግዳል።

የዛሬ መርሃ ግብሮች ሊጉ በኮሮና ምክንያት ሲቋረጥ ሳይካሄዱ የቀሩ ተስተካካይ ጨዋታዎች ናቸው።

ዛሬ አንድ ብሎ ዳግም የሚጀምረው የሊጉ ውድድርም በ40 ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

ፕሪሚየር ሊጉን ከረጅም አመታት በኋላ ለዋንጫ እጅጉን የተቃረበው ሊቨርፑል በ82 ነጥብ ሲመራ፥ ማንቼስተር ሲቲ፣ ሌሲስተር እና ቼልሲ በርቀት ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

በርንማውዝ፣ አስተን ቪላ እና ኖርዊች ሲቲ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።

ሌሎች የአውሮፓ ሊጎች ቀደም ብለው የተጀመሩ ሲሆን፥ የጀርመን ቡንደስ ሊጋ አሸናፊውን ለይቷል።

ባየርን ሙኒክ ትናንት ምሽት ከሜዳው ውጭ ከዌርደር ብሬመን ተጫውቶ በማሸነፍ የቡንደስ ሊጋውን ዋንጫ ለ8ኛ ተከታታይ አመት ማንሳቱን አረጋግጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.