Fana: At a Speed of Life!

የኦሚክሮን ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሀገራት የአዲስ ዓመት በዓል እንቅስቃሴን እየገደቡ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 22፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የኦሚክሮን ስርጭት በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሀገራት የአዲስ ዓመት በዓል እንቅስቃሴን እየገደቡ መሆኑ ተገለጸ።
የፈረንጆቹ አዲስ አመት በሚከበርበት በዚህ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። ባለፉት ሰባት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ7 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል። ይህን ተከትሎም ለአዲስ ዓመት አቀባበል የታቀዱ ዝግጅቶችን ሀገራት በመሰረዝና መጠናቸውን በመቀነስ ላይ ይገኛሉ።
አሁን ላይ የኦሚክሮን ቫይረስ በአለም አቀፍ ደረጃ ስርጭቱ ይቀንሳል ቢባልም በቅርብ ቀናት ውስጥ በዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ እና ሌሎች የአውሮፓ አገሮች የቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ቁጥር ጨምሯል። ይህም መንግስታት የኮሮና ቫይረስ እገዳዎችን እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል ይላል የቲ አር ቲ ወርልድ ዘገባ።
ከግሪክ እስከ ሜክሲኮ፣ ከባርሴሎና እስከ ባሊ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንዳይደረጉ የተከለከሉ ሲሆን፥ በምሽት ክለቦች ላይ የሰዓት እላፊ ገደቦችን መጣላቸው ተገልጿል፡፡
ደቡብ አፍሪካ በተቃራኒው የተቀመጡ ገደቦችንና ክልከላዎችን ለአዲስ ዓመት ክብረ በዓል ስትል አንስታለች። በሀገሪቱ የበሽታው ወረርሽኝ መጠን የመጨረሻውን ጫፍ ነክቶ እየወረደ በመሆኑ ለአዲስ ዓመት እስከ እኩለ ሌሊት የነበረውን የሰዓት እላፊ ገደብ ወደ 4 ሰዓት ማውረዷን አስታውቃለች፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.