Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል የአምስት አመታት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ከ222 ሚሊየን ብር በላይ የአምስት አመታት የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኦሮሚያ እና የሱማሌ ክልል የሰላም እና የልማት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በጋራ የምክክር መድረኩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴን ጨምሮ የክልል እና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች ተገኝቷል፡፡

በምክክር መድረኩ ሁለቱን ክልሎች በሰላምና ልማት በተሻለ መልኩ ለማስተሳሰር የሚረዳ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ስምምነቱንም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ፈርመዋል፡፡

የሰላም እና የልማት የጋራ ምክክር መድረኩ ለ5 ዓመታት የሚቆይ ይሆናል፡፡

ስምምነቱ የሰላምና የልማት ችግሮችን በሁለቱ ክልል አጎራባች 12 ዞኖች እና 48 ወረዳዎች ለመፍታት ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ለዚህም 222.7 ሚሊየን ብር ስራ ላይ ይውላል ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.