Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል የሴቶች የሰላም ፎረም በአዳማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልል ሴቶች የሰላም ፎረም በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በአዳማ እየተካሄደ በሚገኘው ፎረም ላይ የሁለቱ ክልል ተሳታፊዎችን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ተጋባዦች ተገኝተዋል፡፡

በፎረሙ የኦሮሚያ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሁለቱ ክልል ሴቶች የሰላም ፎረም አባላት፣ የኦሮሚያ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ፣ የተመድ የሴቶች ግብረ ሰናይ ድርጅት፣ የተለያዩ የፌደራል እና የክልል ስራ ኃላፊዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

በባህላዊ የሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ዕሴቶች ዙሪያ ላይ የልምድ ልውውጥ ይደረጋል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.