Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲውን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የፓርቲውን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ አደረገ፡፡
ፓርቲው የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት እና ማኒፌስቶ ይፋ የማድረግ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡
መርሃ ግብሩ ህብረ ብሄራዊነት ለጋራ አንድነት በሚል መሪ ቃል መካሄዱ ተገልጿል፡፡
በመርሃ ግብሩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ብልፅግና ማለት ለቅሶ ሳይሆን ማሸነፍ ፤ጨለማ ሳይሆን ብርሃን ፤ሃዘን ሳይሆን ደስታ ፤ረብሽ ሳይሆን ሰላም ነው እንዲሁም የጎለበተ ባህል ያካበተ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልሽ አብዲሳ በበኩላቸው ፓርቲው የመደመርን እሳቤ ይዞ የመጣ ነው ብለዋል፡፡
እንዲሁም የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ፓርቲ ነው፤ የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ነው፤ፓርቲው ያቀደውን አሳክቶ በተግባር የሚያሳይ ነው፣ከትናንት ተምሮ ወደፊት የሚራመድ ነው በዚህም ይለያል ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያዊነት ህብረብሄራዊነት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ብልፅግና ፓርቲ አዲስ ሃይል ጨምሮ የበለጠ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.