Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ለተፈናቀሉ ወገኖች የአይነት ድጋፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል ሴቶች አደረጃጀት እንዲሁም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለመከላከያ ሰራዊት እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከአይነት ድጋፍ በተጨማሪ ከ22 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ከክልሉ ሴቶች አደረጃጀት ጋር በመተባበር በአምስተኛ ዙር ድጋፉ 100 ሰንጋዎችን ጨምሮ ከ12 ሚሊየን ብር ባለይ ገንዘብ ለመከላከያ ሰራዊት ማስረከቡን የድጋፍ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ፈይሳ ተናግረዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤት የኮሙኒኬሽን ባለሙያ አስቻለው ታደሰ እንደገለጹት÷ በአፋርና በሸዋሮቢት ግንባር 1ሺህ 296 ኩንታል ብርቱካን፣ 8 ሺህ 592 እሽግ ውሃ፣ አምስት ሮቶ ውሃ ከነተሳቢው በመስጠት ሁለቱ ሮቶ ጦርነቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በቋሚነት እዛው እንዲሰራ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የአሮሚያ ክልል ሴቶች አደረጃጀት በ3ኛ ዙር ድጋፉ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የደረቅ ምግቦች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የክልሎች የድጋፍ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ተመስገን ቡርቃ እንደተናገሩት÷ የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ የቆሙበት ወቅት መሆኑን ጠቁመው÷ ድጋፍ ለሚያደርጉ አካላት ሁሉ ምስጋና ይገባል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የ10ሚሊየን 400 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በክልሉ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚሆን የምግብና የአልባሳት እንዲሁም ለጀግናዉ የመከላከያ ሠራዊት ደግሞ የሰንጋ እና የታሸገ ውኃ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ እንደገለጹት÷ በአፋር በተሰራው ጀግንነት የጅቡቲ ኮሪደር እንቅስቃሴ ሳይስተጓጎል አገራዊ የሎጅስቲክስ እንቅስቃሴን ማከናወን ተችሏል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በዚህ ወሳኝ ወቅት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ያደረገዉ ድጋፍ መቼም የማይረሳ እንደሆነ ገልፀዉ÷ ይህንን ትልቅ አጋርነታቸዉን ለክልሉ በማሳየታቸዉ በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ሰራተኞች የተውጣጣ ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቃዮች የሚሆን ከ2 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብና የውኃ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

 

ድጋፉን የተረከቡት የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ፅፈት ቤት ሀላፊ አበባው መሠለ እንደገለጹት÷ በቀጣይ ተፈናቃዮችን ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

 

በኤልያስ ሹምዬ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.