Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ዛሬ ለአርሶ እና አርብቶ አደሮች እንዲሁም ለዘርፉ ተዋናዮች እውቅና ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኦሮሚያ ክልል ለ607 ግንባር ቀደም አርሶ እና አርብቶ አደሮች እንዲሁም ለዘርፉ ተዋናዮች እውቅና ሰጥቷል።

የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራሙ ዛሬ በአዳማ ከተማ አባ ገዳ አዳራሽ ተካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳባ ደበሌ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በእውቅና መድርኩ ላይ ንግግር ያደርጉት የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሀላፊ ዳባ ደበሌ፣ለሽልማቱ የበቁ አካላት የተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እንደነበሩ ገልጸው፤ ሆኖም ግን ውጤት አምጥተዋል ብለዋል።

የኮቪድ-19 ወርርሽኝ፣ የአንበጣ መንጋ ፣ የጎርፍ ክስተት አልፎ አልፎም ቢሆን የጸጥታ ችግር ያጋጠሙ ፈተናዎች እንደነበሩ ያወሱ ሲሆን፣ ፈተናውን ሁሉ ተቋቁመው በግብርና ውጤት ላመጡት አቶ ዳባ ደበሌ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለሽልማት የበቁት 607 አካላት ከአርሶ አደር፣ከአርብቶ አደር፣ከሴቶችና ወጣት ማህበራት፣ከምሁራንና ሌሎችንም ያማከለ ሲሆን፤ የተቀመጠውን መስፈርት ያሟሉ በጥራት ተመርጠዋል ብለዋል ።

ተሸላሚዎቹ ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የዚሁ መርሀ ግብር አንዱ የሆነው የግብርና ዉጤቶችና ሜካናይዝድ ቴክኖሎጂ ባዛርና አዉደ ርዕይ በትላንትናው ዕለት ተከፍቷል።

በአዳነች አበበ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.